መነሻ ገፅ

እንኳን ወደ ድርሻዬ የኦንላየን ትምህርት መስጫ ማዕከል በደህና መጡ?

ድህረገፃችን የኦንላየን ትምህርት በአማርኛ በቀጥታ ማለትም በቨርችዋል ክላስ የሚያስተምር በአይነቱ የመጀመሪያ የሚባል ዌብሳይት ነዉ፡፡ ይህዉ ዌብሳይት ከቤዚክ የኮምፑይተር አጣቃቀም ጀምሮ አድቫንስ የሆኑ የፕሮግራሚንግና የመልቲሚዲያ አፕሊኬሽን ሶፍትዎሮችን በቀጥታ ለመማር ያስችለዎታል፡፡ በአማርኛ የሚሰጠዉ ይህዉ ትምህርት እንደ ሁሉም ሰዉ የእዉቀት ደረጃ የተለያዩ ክፍሎች ያሉት ሲሆን ግለሰቦች የራሳቸዉን የእዉቀት ደረጃ ገምግመዉ መማር ይችላሉ፡፡ ትምህርቱ የእድሜና የጾታ ልዩነት የሌለዉ ሲሆን ማንም አማርኛ ተናጋሪ በትምህርቱ ላይ መሳተፍ ይችላል፡፡

የትምህርቱ ተከታታዮች የሚያገኙት ጥቅሞች

 • በአማርኛ ቋንቋ ትምህርቱ መሰጠቱና ብዙዎች እንጊሊዘኛ ወይም ሌላ ቋንቋ ባለመቻላቸዉ መማር ላልቻሉና ኮመፒዩተርን ለመጠቀም የተቸገሩ ሰዎች በቀላሉ መማር መቻላቸዉ፡፡
 • የትምህርቱ ተከታታዮች ረጅም መንገድ ሳይጓዙና እቤታቸዉ ቁጭ ብለዉ በኢንተርኔት ብቻ መማራቸዉ ካላስፈላጊ መጉላላትና ወጪ መዳናቸዉ፡፡
 • በጣም ትንሽ በሚባል ክፍያ እንደ ምርጫቸዉ በአጭር ወይም ረጅም ጊዜ በአማራጭ ትምህርቱ መሰጠቱ፡፡
 • ያሉበት የእዉቀት ደረጃ የሚለኩበት ሁኔታ በመኖሩ ካሉበት ደረጃ ከፍ ወዳለ የእዉቀት ማማ ለመደረስ የሚያስችሉ የተለያዩ የትምህርት አይነቶች መኖራቸዉ፡፡
 • ትምህርቱ በቀጥታ መሰጠቱ ተማሪዎች በመሃል ያልገባቸዉን ነገሮች ጠይቀዉ መረዳት መቻላቸዉ፡፡
 • ተማሪዎች መከታተላቸዉን ለማረጋገጥ ያልተንዛዙና እዉቀትን ብቻ የሚያረጋግጡ ፈተናዎችና አሳይመነቶች መኖራቸዉ፡፡
 • ትምህርቱን ለብዙ ሰዎች ለማድረስ ይረዳ ዘንድ የተለያዩ የማበረታቻና የማነቃቂያ መንገዶች መኖራቸዉ ይህም
  • አንድ ተማሪ ሌላ ተማሪ ሲያመጣ 10 በመቶ ከሚከፍለዉ ወርሃዊ ክፍያ ላይ ቅናሽ መደረጉና ይህዉም ባመጣዉ ሰዉ ቁጥር በዛዉ ልክ የሚጨምር ይሆናል፡፡
  • ካጠቃላይ ገቢዉ 10 በመቶዉን በኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚገኙ ወላጅ አልባ ህፃናትና ጧሪ አልባ አረጋዊያን መርጃ እንዲዉል ግልፅ በሆነ መልኩ የሚሰጥ  በመሆኑ፡፡ ስለዚህም ከትምህርቱም ጎን ለጎን ወገንን የመርዳት እሴት ያለዉ መሆኑ፡፡
  • በወር ዉስጥ ሁሉንም የትምህርት ክፍሎች ሳይቀሩ ለሚማሩ ተማሪዎች ከሚቀጥለዉ ክፍያ 10 በመቶ ቅናሽ መደረጉ፡፡
 • በትምህርቱ መጠናቀቅ ጥሩ ዉጤት ለሚያመጡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት መኖሩ፡፡
 • በአንድ ክፍለ ጊዜ ከ 10 ሰዉ በላይ አለመኖሩና እርስ በእርስ የመወያየትና ችግሮችን በጋራ የመፍታት አሰራር መኖሩ፡፡
 • በትምህርቱ አንድ ሰዉ ስለኮምፒተር ያስፈልገዋል ተብሎ የሚታሰቡ ትምህርቶች በሙሉ በክፍል ተከፋፍለዉ ስለሚሰጡ ተማሪዎች ከክፍል ክፍል በማደግ ከጀማሪ እስከ ፕሮፌሽናል ደረጃ መድረስ መቻሉ፡፡

ዛሬዉኑ ይመዝገቡና ትምህርቱን ይጀምሩ የተለያዩ ክፍሎችን ማየት ከላይ የሉትን መስፈንጠሪያዎች/ሊንኮች/ ይጠቀሙ፡፡